የልጅነት ጋብቻ (Child marriage)
የልጅነት ጋብቻ ትርጉም
የልጅነት ጋብቻ ማለት በአንድ አገር ህግ ለሴቶችና ለወንዶች ዝቅተኛ ተብሎ የተደነገገውን የጋብቻ ዕድሜ ገደብ በመጣስ የሚፈፀም ጋብቻ ነው፡፡ ይህ ዝቅተኛ የዕድሜ ገደብ የሚደነገገው አንድ ሰው ጋብቻ የሚያስከትላቸው ሃላፊነቶች ለመሸከም የአካል ብቃትና የአዕምሮ ብስለት ያገኛል ተብሎ በሚገመትበት ዕድሜ ነው፡፡ተሻሽሎ በወጣው የፌዴራልና የአማራ ክልል የቤተሰብ ህግ መሠረት ከ18 ዓመት በታች በሴትም ሆነ በወንድ ላይ የሚፈፀም ጋብቻ ሁሉ የልጅነት ጋብቻ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡
የልጅነት ጋብቻ አይነቶች
የልጅነት ጋብቻን በተመለከተ በተደረገው ጥናት መሰረት አራት አይነት የጋብቻ አፈፃፀም እንዳሉ ያመላክታል፡፡ እነሱም፡-
- የቃል ኪዳን ጋብቻ (promissory marriage)፡- የዚህ አይነቱ ጋብቻ በሁለት ቤተሰቦች መካከል ህፃናት ሳይወለዱ ወይም ከተወለዱ በኋላ “ልጅህን ለልጄ” በሚል ቃል የሚፈም ጋብቻ ነው ፡፡
- የህጻንነት ጋብቻ (Child marriage)፡-
የህጻናት ጋብቻ ዕድሜያቸው ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች የሚፈፀም የጋብቻ ስነሥርዓት ነው። በዚህ አፈጻጸም ልጅቱ ዕድሜዋ 12 ዓመት እስኪሞላት ድረስ ወይም ቤቷን ማስተዳደር እስከምትችል ድረስ በአማቶቿ ቤት ትቆያለች፡፡ሙሽራዋ በአማቶቿ ቤት በምትቆይበት ጊዜ ከባድ የሥራ ጫናና የተለያዩ ግዳጆችን ማከናወን ይጠበቅባታል።ከባሏ ጋር ባንድ አካባቢ በመኖራቸው ምክንያት በእርሱም ሆነ በሌሎች ወገኖች ተገዳ የመደፈር ዕድሏ ከፍተኛ ነው፡፡
3. የማደጎ ጋብቻ (Early adolescent marriage):-
ይህ የጋብቻ አይነት የሚፈፀመው ዕድሜያቸው ከ10 እስከ 14 ዓመት ባሉ ተጋቢዎች ነው፣ ከጋብቻው ስነ ስርዓት በኋላ ሙሽራዋ ወደ ሙሽራው ቤት እንድትመጣና ጋብቻ የሚያስከትለውን ግዴታ ሁሉ እንድትወጣ
የምትገደድበት ነው፡፡
4. የጉርምስና ጋብቻ ( Late adolescent marriage)፡-
ከ15-18 ዓመት
ባሉ ህፃናት ላይ የሚፈፀም ጋብቻ ሲሆን ውጤቱ ከማደጎ የጋብቻ አይነት የሚለይ አይደለም፡፡
የልጅነት ጋብቻ አለማቀፋዊ ፣ሃገራዊና ክልላዊ ገፅታና ስርጭት
ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ የልጅነት ጋብቻ ከሚተገበርባቸው ዋና ዋና 25 ሃገራት ውስጥ አንዷ ናት፣ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ደግሞ በ19ኛ ደረጃ ላይ
ትገኛለች፣ በተለይ በአማራ ክልል የልጅነት ጋብቻ መጠን በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ በሃገሪቱ ካሉ ክልሎች የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል፣በክልሉ 48 በመቶ ገጠርና 28 በመቶ በከተማ ያገቡ ሴቶች ጋብቻቸውን የፈጸሙት ዕዴሜያቸው ከ15 ዓመት በታች ነው፣ስለሆነም የልጅነት ጋብቻ በአማራ ክልል
እጅግ የተስፋፋ እና ስርጭቱ ከፍተኛ መሆኑን ከዚህ መረጃ መረዳት ይቻላል፣
የልጅነት ጋብቻ የሚፈፀምባቸው ምክንያቶች
ወላጆች ሴት ልጆቻቸውን ያለእድሜያቸው የሚድሩባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ሀ) የቆየ ወግንና ስርዓትን
ለመጠበቅ
ህ/ሰቡ የልጅነት ጋብቻ በልጆች ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ጥቅምና ጉዳት ጠንቅቆ ካለማወቅ የተነሳ የቆየ ወግንና ስርዓትን ለመጠበቅ በሌላ መልኩ
በልጅነት ካልተዳሩ ቆሞ ቀር ስለሚባሉና በማህበረሰቡ ዘንድ እንደነውር
ስለሚቆጠሩ የራሳቸውን ሆነ የቤተሰባቸውን ክብርና ተቀባይነት እንዳይቀንስ፣
ለ) ምጣኔ ሃብታዊ/ኢኮኖሚያዊ/ ጠቀሜታን ለማግኘት ጋብቻ እንደ አካባቢው ሁኔታ መሬት፣ የቀንድ ከብቶች፣ ጥሬ ገንዘብና የተለያዩ ቁሳቀሱ በጥሎሽ፣ በስጦታ፣ወዘተ የሚለዋወጡበት ስርዓት ስለሆነ፣ በመሆኑም ይህን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማግኘት ሲባል ወላጆች ልጆቻቸውን ያለዕድሜያቸው ይድራሉ፣
ሐ ለወደፊት
አስተማማኝ የኑሮ ዋስትና ለማግኘት ወላጆች የልጆቻቸው
የወደፊት ህይወት እነርሱ አርጅተው ሳይሞቱ የተሳካ ይሆናል በሚል አመለካከት ነው ፡፡
መ) ውድድር በአንድ ማህበረሰብ
ውስጥ የሚኖሩ ወላጆች ቤተሰቡን የሚደግፍና የኑሮ ደረጃን የሚያሻሽል፣ ለቤተሰቡ አለኝታ የሆነ አኩሪና መከታ የሚሆን አማች ለሴት ልጆች ለማግኘት በመሽቀዳደም ልጆቻቻውን ያለዕድሜያቸው ይዳራሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በተለይ አርሶ አደር ቤተሰቦች ኑሩአቸውን ለማሻሻልና ደረጃቸወን ለማሳደግ እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነታቸውን ለማስፋት የተሻለ
የኑሮ ደረጃ ካለው ቤተሰብ ወይም ጎሳ ጋር ለመዛመድ ሲሉ የጋብቻ ዝምድና መፍጠር ስለሚፈለጉ ያለእድሜአቸው ይድሩአቸዋል፡፡
ሰ)ክብረንፅህናን ጠብቆ ለማቆየት
በወላጆች
በኩል የሚንጸባረቁ አስተሳሰቦች በጋብቻው ወቀት ክብረ-ንፅህና ከሌላት ድርጊቱ በርሷም ሆነ በቤተሰቧ ላይ
ሃፍረትና ውርደትን ያስከትላል፡፡ ከዚህም አልፎ ግርፊያ የሚደርስባት ሲሆን ወላጆቿ የተቀበሉትን ጥሎሽ ወይም ሰጦታ በሰርጉ ዕለት እንዲመልሱ ይደረጋል፡፡እርሷም ከባሏ ቤት ትባረራለች፡፡ ጋብቻም ወዲያውኑ ይፈርሳል፡
ረ) ብዙ ልጅ ለማፍራት
ልጃ ገረዶች በልጅነት ዕድሜያቸው ተድረው መውለድ ከጀመሩ በርካታ ልጆች ሊወልዱ ስለሚችሉ ወላጆች ብዙ የልጅ ልጆች በማግኘት ሲሉ፣
አካላዊ ለውጥ
በአንዳንድ የክልላችን
አካባቢዎች ሴት ልጆች በኮረዳነት ዕድሜ ደርሰው አካላዊ ለውጥ ማሳየት
ሲጀምሩ ካልተዳሩ እንደነውር ይቆጠራል/ ደ/ወሎ-ወረባቡ/፣ በመሆኑም ሴት ልጅ ጡቷ ከወደቀ
ጠያቂ አይኖራትም ስለሚባል ሳይደርሱ ይዳራሉ በሌሎች አካባቢዎች
ሴት ልጅ የወር አበባ ካየች የቄስ ሚስት አትሆንም በሚል የተሳሳተ አመለካከት ሴት ልጆች በህፃንነታቸው ይዳራሉ፣
ሸ) ብድር /አቆልuይ/ ለመመለስ
በጋብቻ ወቅት ሰረግ ከዚህ ቀደም ወዳጅ ዘመድ፣ጎረቢት፣Õደኛ፣ ወዘተ ሲያደርጉ
በጥሬ ገንዘብ ሆነ በሌላ መልኩ ያበረከቱትን ብድር ለማስመለስ፣ከማን አንሳለሁ በማለት፣
ቀ) በአቅራቢያ ትምህርት ቤቶች አለመኖር
የ2ኛ ደረጃ
ትምህርት ቤቶች በሌሉባቸው አካባቢዎች ሴት ልጆች ቤት ተከራይተው በሚማሩበት ወቅት ጾታዊ ተፅዕኖ፣ መደፈርና ጠለፋ ይደርስባቸዋል በማለት፣ ከጋብቻ በፊት ለሚደረግ ወሲብ ያላቸው አመለካከት መለወጥ ላልተፈለገ እርግዝና ይዳርጋቸዋል ብሎ በመፍራት፣
በ)ድርቅ
በአንዳንድ
እርጥበት አጠር ወረዳዎች የሰብል ምርት በየአማቱ እንደ ልብ ስለማይገኝ ምርት በጨመረ ወቅት ሴት ልጆች ተሰብስበው በአንድ ላይ ይዳራሉ፣
ተ) ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች
የጠለፋ ጋብቻን በመፍራት፣
ዘመድ አዝማድና ጎረቤትን ጠርቶ የሰርግ ድግስ ለመብላትና የአካባቢው ባህል የሚጠብቀወን ወግና ማዕረግ ለማVላት፣
ድል ያለ ድግስ በመደገስ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ዝና ለማግኘት፣
በአካባቢው
የመጀመሪያው ልጅ ዳሪ ለመሆን፣
ያለዕድሜ ጋብቻ የሚያስከትላቸው ችግሮች
- በአካልና በጤና ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች
አርግዛ ለመውለድ በአካልና በስነ-ልቦና ያልዳበረች ስለሆነች በእርግዝናና በወሊድ ጊዜ የተለያዩ የጤና ችግሮች ትጋለጣለች፤ በአቅም ያልተመጣጠነ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ በረጅምና በአስቸጋሪ ምጥ ምክንያት ለፌስቱላ መጋለጥ፤ በሕፃንነት ዕድሜ አርግዘው የሚወለዱት በዕድሜ 20-24 ሆኗቸው ከሚወለዱት በወሊድ
የመሞት ዕድላቸው እጥፍ ነው፡፡ ጤንነቱና መሠረታዊ ፍላጐቱ ያልተሟላ ቤተሰብ ይፈጠራል፡፡
ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች
የትዳርን ምንነት በሚገባ ጠንቅቆ ለማወቅና ሃላፊነትም ለመሸከም አካላዊናም ሆነ ስነ-ልቦናዊ ብስለት ዝገጁነት ስለማይኖራቸው ለበርካታ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች የተጋለጡ ናቸው፡፡
የትዳርን ሃላፊነት በአግባቡ መሸከም አለመቻል ስነ-ልቦናዊ ጫና በራስ መተማመንና ውሳኔ ሰጭነትን ሚና ይቀንሳል፡፡
ራስ በራስ ልጆችን መውለድና ያልተመጣጠነ የቤተሰብ ቁጥር መኖር፣ ልጆችን በአግባቡ ማሳደግ አለመቻል፣ በሚወለዱ ልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል አገሪቱ ላይም እንዲሁ፤የወንድ የበላይነት የሰፈነበት ትዳር ይፈጠራል፣ ያልተረጋጋ ትዳር /ፍች/ ልጆች በአንድ ወላጅ/ያለ ወላጅ የማደግ ዕድል ይገጥማቸዋል፡፡ከገጠር ወደ ከተማ ፍልሰት፣ ሴተኛ አዳሪነት ፣ ጐዳና ተዳዳሪነት፣ የቤት ሠራተኝነት ለወሲባዊ ጥቃቶች፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለጉልበት ብዝበዛ ….ወዘተ ይጋለጣሉ፤ጭንቀት፣ ውጥረት፣ እንዲሁም ለፊስቱላ የተጋለጡ ልጆች በማህበረሰቡና በቤተሰብ መገለልና አድሎ ይፈፀምባቸዋል፡፡
ያለ እድሜ ጋብቻን በተመለከተ የኢትዮጵያ ህግ ምን ይላል?
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ መሰረት ጋብቻ የሚፈቀደው የሁለቱም ተጋቢዎች እድሜ 18 አመት ሲሆን መሆኑ ይታወቃል፡፡ነገር ግን ከዚህ እድሜ በታች በሁለቱም ፆታዎች የሚፈፀም ጋብቻ ጐጅ ልማዳዊ ድርጊትና የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡
መሆኑም አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው የእድሜ ገደብ ውጭ ማንም ሰው አስቦ ለአካለ መጠን ያልደረሰችንውን ልጅ ያገባ እንደሆነ
ሀ. የተበዳይዋ/ የተጋቢዋ/ እድሜ 13 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ጽኑ ስራት ወይም
ለ. የተበዳይዋ/ ተጋቢዋ / እድሜ ከ13 ዓመት በታች ከሆነ እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 648 ላይ ተደንግጓል፡፡
No comments:
Post a Comment