በአማራ ሴቶች ማህበር በተዘዋዋሪ ብድር የገቢ ማስገኛ ፕሮግራም እንቅስቃሴና የመጣ ለውጥ
ፕሮግራሙ
በአጠቃላይ እንደክልል ሲታይ እያመጣ ያለው ለውጥ አበረታች ነው፡፡
ለምሳሌ
ያህል ብድር ከወሰዱት 5254 ተጠቃሚዎች ውስጥ 5184 ተጠቃሚዎች
በየወሩ ብድር መመለስ መጀመራቸው፣
ብድር
ከሚመልሱት ተጠቃሚዎች ውስጥ 4107 ተጠቃሚዎች የተበደሩት ብር ሰረተው በመለወጣቸውና ትርፋማ በመሆናቸው ሙሉ በሙለ (100%)
መመለስ መቻላቸው፣
በክልል
ደረጃ አስካሁን ጭራሽ በድር መመለስ ያልጀመሩ 73
እያቆራረጡ
የሚመልሱ 1074 መሆናቸውየሚጠቀስ ነው፡፡
እንዲሁም ተጠቃሚዎች የቁጠባ ባህላቸውን ማሳደግ በመቻላቸው ከ1000 እስከ 8000 ብር ድረስ መቆጠብ
መቻላቸው፣ (አዊ፣ምስ/ጎጃም፣ምዕ/ጎጃም፣ደሴ፣ሰ/ጎንደር፣ሰ/ሸዋ፣ደ/ብርሃን) ያሉ ተጠቃሚዎች
ባገኙት
ብድር መስራት በመቻላቸው ከ2000.00 እስከ 11000.00 ብር ድረስ መቆጠብ መቻላቸው፣(ጎንደር ከተማ)
ባህርዳር
ከተማ በዚህ ብድር ተነስተው በርካታ ሴቶች 8000.00 እስከ
40000.00 ድረስ መቆጠብ መቻላቸው፣ ቤተሰባቸውንም መምራት መቻላቸው፣
የሴቶችን
የስራ ባህልን ማሳደግ የተቻለ መሆኑ፣
ቤተሰባቸውን
መምራት፣ማስተማርና ባለፈ ከተጋላጭነት የወጡበት ነው

No comments:
Post a Comment