Tuesday, March 21, 2017

የሴቶች የመሬት ባለቤትነት መብት ማስከበርና የሴቶችን ጥቃት ማስቆም ፕሮጀክት



የሴቶች የመሬት ባለቤትነት መብት ማስከበርና  የሴቶችን ጥቃት ማስቆም ፕሮጀክት

ኢትዮጵያ ያሳለፈችው ረጅም ጊዜ የታሪክ ዘመናት የአገሪቱ ፖለቲካል ኢኮኖሚ  መሰረታዊ አጀንዳ ሆኖ የቆየና አሁንም ቁልፍ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚና  ማህበራዊ  መወያያ ሆኖ የሚገኘው የመሬት ይዞታና የመሬት ባለቤትነት ፣የመሬት ይዞታ  እና የመሬት አጠቃቀም ጉዳይ ነው፡፡በፌደራልና በከልል መንግስታት በወጡ የህግ ማዕቀፎች መሰረት አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ በተለይም ሴቶችና ህፃናት መሬት በነፃ የማገኘትና የመሬት ባለይዞታ የመሆንና መሬቱን የመጠቀም መብት ተግባራዊ  በማድረግ ሂደት በየአካባቢው የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮች እንዳሉና እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍና ህገ መንግስቱን የህግ ማዕቀፎች መሰረት በማድረግ ተገቢውነ ውሳኔ በመስጠት በኩል የፍትህ አካላት፣የገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር የሴቶች ማህበርና የሴቶች ህፃናት ጉዳይ ተቋማት የማይተካ ፋይዳ እንዳላቸው ግልፅ ነው፡፡
Ø ለግል ባለቤትነትና ሰፊ ዕውቅና እና ጠበቃ የሰጠው የኢፊዲሪ ህገ መንግሰት የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ እንደሆነ እና መሬት የማይሸጥ፣የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብ\ሄር ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ሀብትና ንብረት እነደሆነ በአንቀፅ 40 ንዑስ አንቀፅ 3 በግልፅ ይደነግጋል፡፡
Ø ህገ መንግስቱ የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት የግል ባለቤትነት የማይያዝ መሆኑን ከመደንገጉ በጠጨማሪ ለአርሶ አደሮች መሬት የማግነኘት መብት፣እውቅናና ጥበቃ ሰጥቷል፡፡
Ø ከዚህ አንፃር፣
Ø አርሶ አደሮች መሬት በነፃ የማግኘትና መብት እንዳላቸው እና ከመሬታቸውም ያለመነቀል መብት ያላቸው መሆኑ፣
Ø መሬት የመንግስትና የህዝብ መሆኑ ሳይነካ የግል ባለሀብቶች በመንግስት የሚወሰነውን ክፍያ እየከፈሉ ማልማትና መጠቀም መብት እንዳላቸው፣
Ø ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጉልበቱ ወይም በገንዘቡ መሬት ላይ የሚገነባው ቋሚ ንብረት ወይም በመሬቱ ላይ ለሚያደርገው ማንኛውም መሻሻል ሙሉ መብት ያለው መሆኑ፣የማከራየት፣የመለወጥ፣የማውረስ መብቶችን ያጠቃልላል፡፡
Ø በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 40 ንዑስ አንቀፅ 4 እስከ ንዑስ እንቀፅ 8 የተደነገጉት ድንጋጌዎች የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን ለኑሮው ዋስትና የሆነውን መሬት በነፃ የማግኘት ፣የመሬቱ ባለቤት /ባለይዞታ የመሆንና ያለበቂ ምክነያት ያለመነቀል መብት እንዳላቸው፣ከመሬቱ የሚነቀሉበት በቂ ምክነያት ባለ ጊዜ መሬቱን በማልማት ላደረጉት ቋሚ መሻሻል እና በመሬቱ ላይ የተከለውን ቋሚ አትክልትና ሰብሎች በቂ ካሳ የማግነት መብት እንዳላቸው፡፡
የመሬት ባለይዞታ የመሆን መብት በፌደራል ህጎች
  የመሬት ባለይዞታ የመሆን መብት በፌደራል ህጎች፣የፌደራል መንግሰት በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የመጀመርያውን የፌደራል የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ በ1989 ዓ.ም አውጥቷል፡፡
   የመጀመርያው አዋጅ 89/1989  ሲሆን የገጠር መሬት ፖሊሲና ስትራቴጊጂ ከተነደፈ በኋላ ፖሊሲውን በአግባቡ ሊያስተገብር በሚችል መልኩ አዋጁን ማሻሻል በማስፈለጉ የገጠር መሬት አጠቃቀምን በተመለከተ የተሸሻለው የፌደራል አዋጅ ቀጥር 456/97 ወጥቷል፡፡
  የነዚህ ህግ ማዕቀፍ፡-
Ø  አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩበነፃ መሬት የማግኘት መብት በማረጋገጥና የአርሶ አደሩን ከይዞታ ያለመፈናቀል ምብት ጥበቃ መስጠት፣
Ø  አርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ከይዞታቸው ማፈናቀል የሚያስፈልግበት በቂ ምክነያት ሲኖር መሬቱን ለማልማት ያወጠውን ወጭና በመሬቱ ላይ ላለሙት ቋሚ ንብረትና ሰብል በቂ ካሳ የሚያገኙበት ሁኔታ በዝርዝር በመደንገግ የህገ መንግስቱን መሰረታዊ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የህግ መሰረት ጥለዋል፡፡
መሬት በነፃ የማገኘትና የይዞታ መሬትን የመጠቀም መብት በክልል የህግ ማዕቀፎች
  የፌደራል መንግሰት በህገ መንግስቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት አዋጅ ቁጥር 4546/1997 የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ያወጀ ሲሆን በእምቀፅ 17 ንዑስ አንቀፅ 1 የፌደራል መንግስት ያወጠውን አዋጅ ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን የሚያወጣ ስለመሆኑ በክልል ምክር ቤት በኩል የሚወጣ ስለመሆኑ ይደነግጋል፡፡
  በመሆኑ በክልሉ መንግስት በኩል የወጡ  ህጎች
1)  መሬት የማገኘት መብት፡-በክልሉ ያለ ማንኛውም 18 ዓመት የሞላውና በግብርና ስራ የሚተዳደር የፆታ ልዩነት ሳይደረግ መሬት ማገኘት ይችላል፡፡(5/2)፤ጆቻቸውን ያጡ እድሜያቸው 18 አመት ያልሞላቸው ህፃናታ መሬት በነፃ ማግኘት ይችላሉ፡፡(5/2
2)  መሬት ይዞታን በስጦታ መስተላለፍ፡-አንስተኛ መሬት እያረሰ ያለ ልጅ፣የልጅ ልጅ ወይም ቤተሰብ አባል ከሆነ ፣ተቀባዩ የባለ ስጦታውነ መሬት እያረሰ ወይም ሌላ ስራ እየሰራ ስጦታው ከመሰጠቱ በፊት ለ3 ወራት ይቆጠራል፣16/2
  ሳይናዘዝ ከሞተ በግብርና ለሚተዳደር ወይም ለመተዳደር ለሚፈልግ ልጅ ወይም ቤተሰብ ይተላለፋል፣(16/5)
  ልጅ ወይም ቤተሰብ የሌለው በክልሉ ለሚኖሩ ቤተሰቦቹ (ያላቸው ይዞታ ከፍተኛ ጣራ ያልደረሰ ከሆነ) ሊወርሱ ይችላሉ፣(16/6)
  ወራሽ ያልተገኘለት ቦታ ለአዲስ አመልካቾች ይከፋፈላል፣(16/9)

No comments:

Post a Comment