ማኀበራት/ድርጅት ማለት ምን ማለት ነዉ?
በማህበራዊ ሳይንስ የእንግሊዘኛ ትርጉም መሰረት ድርጅት/አደረጃጀት
“ organization is a highly organized group having explicit
objectives, formally stated rules and regulations and a system of specifically
defined roles, each with clearly designated rights and duties.”
ድርጅት/አደረጃጀት ግልጽ ዓላማ፣በአግባቡ
የተደነገገ ህግና መተዳደሪያ ደንብ ያለው፣እያንዳንዱ አባል በድርጅቱ/ማህበሩ ውስጥ የተወሰነና ግልጽ የሆነ
ሚና ፣በግልጽ የተቀመጡ
መብቶች፣ተግባርና ሃላፊነቶች ያሉት በስርአት የሚመራ በከፍተኛ ደረጃ የተደራጀ የሰዎች ስብስብ ነው፡፡
ልዩ ልዩ የህ/ሰብ ክፍሎች ተመሣሣይ ፍላጎትና ጥቅማቸውን ለማሣካት ሲሉ የአጭርና የረዥም
ጊዜ ግባቸውን በመለየትና ይህንን ለማስፈፀም አቅጣጫዎች በማስቀመጥና ድርጅቱን
(ማኀበሩን )የሚያስተዳድሩበት መርሆዎች የጋራ
ደንቦች ቀርፀው የሚያቋቁሙት የጋራ ፍላጎታቸውና ጥቅማቸውን ማስፈፀሚያ
መሣሪያ ነው፡፡
እንደየ አባላቱ የአደረጃጀት ፍላጐት ማህበራት በሚከተሉት አይነት ሊቋቋሙ ይችላሉ፡፡ለምሣሌ
፡-
ü የብዙኃን ማህበራት / የሴቶች ፣ የወጣቶች ፣ የአርሶ አደሮች ፣ ወዘተ ማህበራት /
ü የሙያ ማህበራት / የመምህራን ፣ የጤና
ባለሙያዎች ፣ የህግ ባለሙያዎች ማህበር … ወዘተ
ü
የህብረት ስራ
ማህበራት / በገቢ ማስገኛ የተሰማሩ ፣ የሸማ
ሰሪዎች ፣ የባልትና ውጤቶች አቅራቢ ህብረት ስራ ማህበር …ወዘተ ፣
ü እነዚህ አደረጃጅቶች ፡-
ü
ለዲሞክራሲ ሥርዓት
ግንባታ ፣
ü
ለፈጣን ልማት መረጋገጥ እንዲያስችል ሰፊውን ህዝብ በተደራጀ መልኩ በማንቀሣቀስ የልማት ቀጥታ ተሣታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ፣
ü የአባላትን መብትና ጥቅም ለማስከበር የጐላ ሚና ስላላቸው በብዛትና በጥራት እንዲፈጠሩና እንዲጠናከሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ተገቢ ነው፡፡
ü በግሎባላይዜሽን ዘመን መንግስት ብቻውን ልማቱን
በማካሄድ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት እና የዜጐቹን ፍላጎት ለማሟላት ይቻላል ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም፡፡
ስለሆነም ከድህነት እሽክርክሪት ( poverty Cycle ) ለመውጣት ህ/ሰቡ በሚፈለገው የህዝብ አደረጃጀቶች እንዲደራጅ ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡
- ሴቶች ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ወጥተው የራሳቸው ሃብትና ንብረት እንዲያፈሩ
በሙያቸው፣ በጾታቸውና
በእድሜያቸው በሌሎችም በጋራ ሊሰሩባቸውና ሊታገሉባቸው በሚችሉበት አደረጃጀቶች ተደራጅተው ያሉባቸውን መሰረታዊ ችግሮች ለመፍታት አስፈላጊ ናቸው፡፡
መደራጀት አስፈላጊ ነው ከምንልባቸው አሳማኝ ምክንያቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ፤
ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በተደራጀ መልክ ለማስጠበቅና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማስከበር፣
በህይወት የመኖር፣፣በአካሉ ግዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣የመሰብሰብ
የመምረጥ መመረጥ ወዘተ
ሕገ መንግስታዊ መብትን ለማስከበር / ሕገ. መ.
አንቀፅ 31 ንዑስ አ.1 / «ማንኛውም ሰው
ለማንኛው ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት
ሰጥቷል» ፣
በየደረጃው ያሉ መንግስታዊ አካላት በሚያወጧቸው ፖሊሲዎች ፣
መመሪያዎች ሕጐችና ደንቦች የህብረተሰቡን
ተሣታፊነትና ተጠቃሚነት ያካተቱና የሚያረጋግጡ ስለመሆናቸው አውንታዊ ተጽዕኖ ለማሣረፍ ፣
በተናጠልና በግል ሊፈቱ
የማይችሉ ጉዳዩች በመተባበር መፍትሔ እንዲያገኙ ለማድረግ ፣
በፆታ ምክንያት የሚፈጠሩ አድሉአዊ አሠራሮችንና በደሎችን እንዲወገዱ ለመታገል፣
የሙያ ብቃትን ለማሣደግ ሙያን ለማስከበር፣
እንዲሁም በሙያቸው የሚጠበቅባቸውን አስተዋጾ ለሀገር
እንዲያበረክቱ
ጎጂ ልማዳዊ
ድርጊቶችን ለማስወገድና ጠቃሚ ባህሎችን በማጎልበት በኩል ጉልህ ሚና ለመጫዎት፣
የማኀበረሰብ ንቅናቄ
በተደራጀ መልኩ በመፍጠር የሴቶችን
ተሣታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሣደግ፣
ገንዘብ፣እውቀትንና ጉልበትን በጋራ አቀናጅቶ በመጠቀም ተጨባጭ ልማታዊ ለውጥ ለማምጣትና ከሚገኘው ጥቅም በቀጥታ ተጠቃሚ ለመሆን፣
የጋራ ጉዳዮቻቸውን የሚመክሩበትና አቋም የሚወስዱባቸውን መድረኮች ለመፍጠር፣
በአካባቢ በሚካሄዱ የልማት እንቅስቃሴዎች
እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ የተደራጀ አቅም በመፍጠር መሣተፍ እንዲቻልና ከሚገኘው ውጤትም ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ፣
የተለያዩ ማህበራት መኖር ጠንካራና በመልካም አስተዳደር የተገነባ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲፈጠር አጋዥነታቸው የጐላ ስለሚሆን፣
የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነትና ተሣታፊነት
የሚያረጋግጡ ተጨማሪ አዳዲስ ፖሊሲዎች ሕጐች ፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች እንዲወጡ ሀሣብ በማመንጨት በኩል አስተዋጽኦ ለማድረግ፣
ከመንግስትና የተለያዩ አካላት የተለያዩ የአቅም ግንባታ ድጋፎችን ለማግኘት… ወዘተ መደራጀት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡