Wednesday, April 12, 2017

ሴቶች የለውጥ ሀዋሪያት እንደሚሆኑም እርግጠኛ ነኝ ፡፡





 















የዛሬ ማንነቴን የቀረፀልኝ በገዳም ያሳለፍኩት ጊዜ ነው፡፡ በአደግኩበት በሀረር የካቶሊክ ገዳም በደስታ የተሞላ የልጅነት ጊዜ አሳልፌያለሁ፡፡ዛሬ የደረስኩበት ደረጃ ለመድረስ ያላለፍኩት እሾህና መሰናክ አልነበረም፡፡ያለወላጆቼ ድጋፍ በገዳም አድጌያለሁ፡፡ልታሳድገኝ የወሰደችኝ አክስቴ የቤት ሰራተኛና የል ሞግዚት አድርጋኝ ነበር፡፡ይህን በትግል  የተወጣሁት ህልም ስለነበረኝ ነው፡፡ ህልሜን እውን ለማድረግም ፈተናዎችን አሳልፌያለሁ፡፡ ዛሬ ግን እዚህ ነኝ፡፡ በህዝብ የሚጎርፍልኝ አድናቆት ምግቤ ነው፡፡ያደግኩት ያለቤተሰብ ፍቅር ነውና፡፡
ሴቶች አቅማቸው አልታየም ብየ አምናለሁ ፡፡ የህልማችን  ለመሆን አቅማችን አጠን እንጠቀም ፡፡ወደፊት የሴቶች ተሳትፎ እንደሚያድግና አገራችን ታላቅ እድገት እንደምታስመዘግብ ከልቤ አምናለሁ ሴቶች የለውጥ ሀዋሪያት እንደሚሆኑም እርግጠኛ  ነኝ ፡፡
ሙሉአለም ታደሰ  
ለተምሳሌት

No comments:

Post a Comment