Monday, November 27, 2017

የአማራ ሴቶች ማህበር የከተማ አባላት በተለያዩ የጥቃቅን የስራ ዘርፎች ተሰማርተዉ ተጠቃሚነታቸዉን ለማጎልበት የይሰራል

የአማራ ሴቶች ማህበር የከተማ አባላት በተለያዩ የጥቃቅን የስራ ዘርፎች ተሰማርተዉ ተጠቃሚነታቸዉን ለማጎልበት ከተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፡፡አባላት በተለያዩ የስራ ዘርፎች (በማገዶ ቆጣቢ ምድጃ፣ በባልትና ዉጤቶች፣ በልዩ ልዩ የግንባታ ዕቃ ማምረት፣ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎት ወ.ዘ.ተ) እንዲሰማሩ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ታቅዶ 7‚286 አባላትን  ወደስራ ማስገባት ተችሏል፡፡ 




በተለይም የጥቃቅን ዘርፍ ስራዎች መነሻ ካፒታል የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ማህበሩ በሁሉም መዋቅሩ አባላት ከህብረት ስራ ማህበራት፣ከአብቁተና ሌሎችም አበዳሪ ተቋማት ብድር አግኝተው ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ  አባላት ያለባቸውን የመስሪያ ገንዘብ (የመነሻ ካፒታል) እጥረት ለመፍታት ጥረት ያደርጋል፡፡ በዚህም ባሳለፍናቸው ሶስት ወራት 6‚961አባላት 1‚271‚600 ብር ብድር እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ 
 አባላት ወደ ስራ የሚያስገባ ብድር ከአበዳሪ ተቋማት እንዲያገኙ ከማድረግ ባለፈ የሚያገኙትን ብድርም ለተባለለት አላማ እንዲያውሉትና በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ከቢዝነስ ፕላንና ስራ አመራር ስልጠና ጀምሮ በመስጠት ውጤታማ ሆነው ነገ ወደ ዘርፉ ለሚገቡ ሴቶች አርአያ ሆነው የተሞክሮ ማሳያ እንዲሆኑ ሙሉና ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ይህን ስራ ሲሰራም ከሚመለከታቸው ተቋማት የሚደረግለት ሙያዊ ድጋፍና ትብብር ማህበሩ ሁሌም ብርታት እንዲሰማው የሚያደርግ በመሆኑ መላው አጋሮቻችን ልናመሰግን እንወዳለን፡፡

No comments:

Post a Comment